ከ3 አመት ፍቅረኛዬ ጋር ልንጋባ ቢሆንም አዲስ ፍቅር ይዞኛል!!!

Written by on December 10, 2018

የምኖረው ከኢትዮጵያ ውጭ ነው፡፡ ከሦስት ዓመት በላይ አብራኝ የቆየች ፍቅረኛ አለቺኝ፡፡ ሃገር ቤት መጥተን ሰርግ ለመደገስ እናስባለን፡፡ ቤተሰቦችም ቀኑን በጉጉት እየጠበቁ ነው፡፡ በቅርቡ ግን ብዙ የማያግባቡን ነገር እየበዙ ነው፡፡ ጭቅጭቃችን በርክቷል፡፡ በዚህ መሃል እኔ ወደ ሃገሬ ለእረፍት በመጣሁበት ከአንዲት ወጣት ጋር ተዋውቄ ፍቅር ውስጥ ገብቼያለሁ፡፡ በፍቅር ከንፈናል ብል ይቀላል፡፡ በእሷ ምክንያት ለሦስት ሳምንት የመጣሁት ሰው ሁለት ወር አለፈኝ፡፡ አብሬያት የምሆነው እዚህ ካሉ ቤተሰቦቼ እየተደበቅኩ ነው፡፡ አዲስ የተዋወቅኳትን ስለፍቅረኛዬ አልነገርኳትም፡፡ ልዋሻት አይገባም ብዬ ስለፍቅረኛዬ ልነግራት እልና እፈራለሁ፡፡ ላጣት አልፈልግም፡፡ ፍቅረኛዬም ደግሞ የምታውቀው በቤተሰብ ጉዳይ ቆይታዬ እንደተራዘመ ነው፡፡ ስመለስ ወደ ጭቅጭቅ ህይወት መመለሱ ያሳስበኛል፡፡ ቤተሰብ ሰርግ ይጠብቃል፡፡ ምኑም ከምኑ እንደምይዘው ግራ ገብቶኛል፡፡ እንዴት ላድርግ?
ዮናታን


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *Current track

Title

Artist