ፍቅረኛዬ ከብዙ ሴቶች ጋር ይታያል…

Written by on December 17, 2018

ፍቅር ከጀመርን ገና አምስት ወራችን ነው፡፡ በሥራው ምክንያት በጣም ብዙ ሠዎች ያውቃል፡፡ ከብዙ ሴቶች ጋርም ግንኙነት እንደነበረው አውቃለሁ፡፡ እርሱ ከእኔ በፊት የነበሩት ፍቅረኞች ሦስት እንደነበሩ ቢነግረኝም ከዚያ በላይ እንደሆኑ እገምታለሁ፡፡ ከብዙ ሴቶች ጋር ይታያል እያሉ ያሙታል፡፡ አንዳንድ ጓደኞቼ በግልፅ “እንዴት ከእርሱ ጋር ትሆኛለሽ” ብለውኛል፡፡ እኔ ግን ያለፈ ታሪኩ አያገባኝም ብዬና ስለምወደውም ጭምር ቀጥያለሁ፡፡ ግን ጫናው ከቤተሰቦቼም ጭምር እየመጣ ሠላም እየነሳኝ ነው፡፡ እስካሁን ያየሁበት ችግር የለም፤ በየሄድኩበት ስለእርሱ ጥሩ ነገር ስለማልሰማ ግን ራሴን መጠየቅ ጀምሬያለሁ፡፡ እየወደድኩትስ ምን ብዬ በቃኝ እለዋለሁ? ብቀጥልስ ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ ምን ይላሉ? ምን ላድርግ?
ኤስ.ቢ.


Reader's opinions

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *Current track

Title

Artist